Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መጣሁኝ

Metahugn

2015 · ትራክ 1 · 6:10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ይኸው ደስ እያለኝ መጣሁኝ ላመልክህ

ምስጋና ይዤ ፣ አምልኮ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ይዤ

ይኸው ዙፋንህ ስር መጣሁኝ ላመልክህ

ምስጋና ይዤ ፣ አምልኮ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ይዤ

አንተ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፫x)

የማመልክህ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

ምስክር ነኝ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

ልከተልህ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

የጠራኸኝ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

ከጫፍ እስከ ጫፍ

ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ

አምላክ ነኝ ባዩ ሁሉ ይሰለፍ

ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው

የኤልያስ አምላክ እርሱ አምላክ ነው

የልቤ ጉልበት ተንበረከከ ይህንን አውቆ

ክብር ሚጋራ ደባሉን ሁሉ በእርሱ አርቆ

የእድሜዬም አፍላ ሽምግልናዬም ለእርሱ ይገዛል

ወዶ እና ፈቅዶ መላው እኔነቴ ክብር ይሰጣል (፪x)

ይኸው ደስ እያለኝ መጣሁኝ ላመልክህ

ምስጋና ይዤ ፣ አምልኮ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ይዤ

ይኸው ዙፋንህ ስር መጣሁኝ ላመልክህ

ምስጋና ይዤ ፣ አምልኮ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ይዤ

አንተ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (፫x)

የማመልክህ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

ምስክር ነኝ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

ልከተልህ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

የጠራኸኝ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)

የእድሜው ልኩ ከእስከ የለው

አልፋ ኦሜጋ እየሱስ ብቻ ነው

ጠቢብ አዋቂው ቢሰበሰብም

በዚህች አይምሮው እርሱ አይለካም

የልቤ ጉልበት ተንበረከከ ይህንን አውቆ

ክብር ሚጋራ ደባሉን ሁሉ በእርሱ አርቆ

የእድሜዬም አፍላ ሽምግልናዬም ለእርሱ ይገዛል

ወዶ እና ፈቅዶ መላው እኔነቴ ክብር ይሰጣል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ