ስላንተ
Selante
2014 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምንድን ነው የመኖር ትርጉሙ የሕይወት ጣዕሙ
ምንድን ነው ሃብትን ማካበቱ ዓለምን ማትረፉ
ምንድን ነው ክብር ዝና ማግኘት ፊደልን መቁጠሩ
ምንድን ነው ውበት ወጣትነት ጉብዝናው ጥቅሙ
አዝማች · Chorus
አንተን ካላከበሩ (፬x)
አንተን ካላከበሩ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምንድን ነው የቃል ዕውቀት እድገት የአገልግሎት ብዛት
ምንድን ነው ቀን ከሌት መሮጡ ሰውን ለማስደሰት
ምንድን ነው በሥጋ ለባሽ መከበር ቅዱሱ መንፈስህ ሳይኖር
ምንድን ነው (፫x)
አዝማች · Chorus
አንተን ካላከበሩ (፬x)
አንተን ካላከበሩ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምንድን ነው ስለእኔ ሳይሆን
ምንድን ነው ሕይወቴ በሙሉ ካላከበረህ እንዲሁ
ምንድን ነው መድከሚ ምንድን ነው ጥቅሙ
ምንድን ነው አላማዬ ካልሆንከኝ ኢየሱስ
ከንቱ ነው (፬x)
ከንቱ ነው (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን ካላከበሩ (ከንቱ ነው) (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አንተን ካላከበሩ (ከንቱ ነው) (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ