ስለስምህ
Selesemeh
2014 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ስለስምህ መልካምነት ማን ተናግሮ ይዘልቃል
ከተባለው በጐነትህ ያልተባለው በዝቷል
በሄድኩበት የምጠራው የአንተ ስምማ
አጠገቤ ብቻ ሳይሆን ለሩቁም ይሰማ (፪x)
ኢየሱስ (፪x) ባልንበት ኧረ ስንቱ ተሰራበት
ማረኝ ብለው ያለቀሱ ስለስምህ ተፈወሱ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ስምህን ስጠራ ሁሌ የማስበው
ትልቁ ተራራ ሜዳ እንደሚሆን ነው
አክብደው ያዩትን የሕይወት መንገድ
ስምህ ባለፈበት ማይሄደው ሲሄድ
ኢየሱስ የነፍሴ መዳኛ
ኢየሱስ የኑሮዬ ዳኛ
ኢየሱስ የሕይወት አክሊሌ
ኢየሱስ ሰማያዊ ክብሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ስለስምህ መልካምነት ማን ተናግሮ ይዘልቃል
ከተባለው በጐነትህ ያልተባለው በዝቷል
በሄድኩበት የምጠራው የአንተ ስምማ
አጠገቤ ብቻ ሳይሆን ለሩቁም ይሰማ (፪x)
ኢየሱስ (፪x) ባልንበት ኧረ ስንቱ ተሰራበት
ማረኝ ብለው ያለቀሱ ስለስምህ ተፈወሱ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የአንተን መልካምነት ይዩ ወንድሞቼ
አላፈርኩምና ስምህን ጠርቼ
በበጐ ተጠሪ ክፋት የማያውቀው
መልካሙ እረኛ ኢየሱስ ብቻ ነው
ኢየሱስ የነፍሴ መዳኛ
ኢየሱስ የኑሮዬ ዳኛ
ኢየሱስ የሕይወት አክሊሌ
ኢየሱስ ሰማያዊ ክብሬ (፪x)
ኢየሱስ (፫x) ኢየሱስ ሰማያዊ ክብሬ
ኢየሱስ የነፍሴ መዳኛ
ኢየሱስ የኑሮዬ ዳኛ
ኢየሱስ የሕይወት አክሊሌ
ኢየሱስ ሰማያዊ ክብሬ
ኢየሱስ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ