ታማኝ ነህ
Tamagh neh
2023 · ትራክ 7 · 7:32 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወዳጅ
በዘመን ሁሉ ይወዳል (X2)
ቸር ወዳጅ
በዘመን ሁሉ ይወዳል (X2)
ቁጥር 1 · Verse 1
ታማኝ ነህ (X4)
ለብቻዬ የነገርከኝ ተፈፀመ
ታማኝ ነህ (X4)
ምድረበዳ የነገርከኝ ተፈፀመ
ምድረበዳ ያወራኸኝ ተፈፀመ
በልጅነት የነገርከኝ ስንት ሆነ
ለብቻዬ የነገርከኝ ተፈፀመ
ስንት ግዜ አሳፈርከኝ ቃልህን ሆነህ
ዛሬ ቆሜ ከቶ ነገን በማያሳይ መንገዴ ላይ
ያኔ መጥተህ እንዲህ አልከኝ አይንህን ከፍተህ እስከሩቅ እይ
ጭው ባለው ምድረበዳ እጄን ይዘህ ያሳመንከኝ
ስንቱን ክብር እያሳየህ በመንገዴ አስደነቅኸኝ አስደመምከኝ
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነህ (X4)
ለብቻዬ የነገርከኝ ተፈፀመ
ታማኝ ነህ (X4)
ምድረበዳ የነገርከኝ ተፈፀመ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምድረበዳ ያወራኸኝ ተፈፀመ
በልጅነት የነገርከኝ ስንት ሆነ
ለብቻዬ የነገርከኝ ተፈፀመ
ስንት ግዜ አሳፈርከኝ ቃልህን ሆነህ
ዛሬ ወንድሜ ልብህ ይበርታ ጌታ ባለህ ነገር ላይ
ሁኔታዎች አያስረሱህ የነገረህን ብቻ እይ
ታማኝ ነው እንደቃሉ ፀንተህ ጠብቅ እያመንከው
ሊያስደንቅህ ሊያስገርምህ ይሄ
አዝማች · Chorus
ጌታ ካንተ ነው (X2)
ብሎአል ወይ
ነግሮአል ወይ
ብሎአል ወይ
ነግሮአል ወይ
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
ብሎአል ወይ
ነግሮአል ወይ
ብሎአል ወይ
ነግሮአል ወይ
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል (X3)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ያለው ዛሬ ይሆናል
እግዚአብሔር ያለው አሁን ይሆናል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ