Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የግድ ታስፈልገኛለህ

Yegid Tasfelegeghaleh

2023 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መንፈስ ቅዱስ ላንተ ያለኝ ትልቅ ቦታ

በምንም አልተካው የኔ እድል ፈንታ

ላንተ አብሮነት ያለኝ ትልቅ ቦታ

በምንም አልተካው የኔ እድል ፈንታ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የምሬን ነው ታስፈልገኛለህ

ሰው እንዴት ትንሽ ነው

ብቻውን ከወጣ ያላንተ

ቀትረ ቀላል ሆኖ

ይኖራል ሁሌ እንደዋተተ

ግን አብሮህ ያለ ሰው

መንፈስህ ያጀበው ከኋላ

ሕዝብን ይታደጋል

በእየሱስ ምድርን እየሞላ

በህይወቴ የነገርከኝ

ያስጀመርከኝ መንገድ

ብቻዬን አልደፍረውም

መንፈስህ ነው የግድ

በሰው አፍ ብቻ አውርቼ

አይደለም የማሳምነው

ወይ ከእግረኛ ጋር ሮጬ

ልድረስበት የምለው

መኖር አልችልም ያላንተ

እኔ አለመድኩም ያላንተ

አገልግሎትም ያላንተ

አይሞከርም/አይደፈርም ያላንተ

(፪x)

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የምሬን ነው ታስፈልገኛለህ

አይቀልብኝ ጌታ አብሮነትህ

ጌታ አብሮነትህ

እኔ አልለምደውም

እየሱስ አብሮነትህን

ጌታ አብሮነትህን

የኔ ሞገስ ክብሬ (አንተ ነህ አንተ)

የኔ ማስፈራቴ (አንተ ነህ አንተ)

እሩቅ የምሄድብህ (አንተ ነህ አንተ)

መቼም የማልቆምብህ (አንተ ነህ አንተ)

እኔ የለመድኩት (ከአንተ ጋር)

የእውነት የምኖረው (ከአንተ ጋር)

አገልግሎቴ (ከአንተ ጋር)

መቼም የማይቆመው (ከአንተ ጋር)

ሀገር የሚሰማኝ (ከአንተ ጋር)

ምድርን የምወርሰው (ከአንተ ጋር)

ጠላት የሚፈራኝ (ከአንተ ጋር)

የማልለመደው (ከአንተ ጋር)

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የግድ ታስፈልገኛለህ

የምሬን ነው ታስፈልገኛለህ

ጣልቃ የማትገባበት የማትሳተፍበት

የሕይወቴ ክፍል የለም

አንተን የማያካትት

እውቅና እሰጥሃለሁ በነገሬ ሁሉ ላይ

ዘንግቼህ አቅም የለኝ

የት ልሄድ አንተን ሳላይ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ