Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመልካለሁ

Amelkalehu

2007 · ትራክ 2 · 6:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነፍሴን ማርከህ ገዝተኀኛል በፍቅርህ

ስለእኔ በደል ዋጋ ከፍለሃል

ዛሬ እኔ ለአንተ ብዘምር ያንስሃል

ፍቅርህን ለመግለጽ ለእኔ ሞተሃል

አመልካለሁ እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ

ቤትህ ይሁን የመጨረሻዬ

አንተን ትቼ አማራጭ አላይም አላገኝም

ዘለዓለም

ምንም የለም ለአንተ ያደረኩት ዉለታ

ምላሽ የሚሆን ፍቅርህን የሚተካ

በፊትህ መቆም ማይገባኝ ነበርኩኝ

ግን በደም ገዝተህ ልጅህ አደረከኝ

አመልካለሁ እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ

ቤትህ ይሁን የመጨረሻዬ

አንተን ትቼ አማራጭ አላይም አላገኝም

ዘለዓለም

የፍቅር አምላክ ነህ

(ነፍስህን የሰጠህ) ነፍስህን የሰጠህ ስለእኔ

(ራስህን አዋርደህ) ራስህን አዋርደህ

አጸዳህ በደሌን

ስለዚህ በሕይወት በኑሮዬ

አንተን አከብራለሁ

ለዘለዓለም አሜን

አመልካለሁ (፱x) (አማራጭ አላይም አላገኝም)

ዘለዓለም

አመልካለሁ (፪x) ጌታ

ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ

አመልክሃለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ