Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመሰግናለሁ

Amesegenalehu

2012 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አመሰግንሃለሁ(፫)

ስትረዳኝ/ስትራራልኝ በዓይኔ ስላየሁ

አመሰግንሃለሁ(፪)

የሚጤሰውን ጧፌን አላጠፋህም

ቅጥቅጡን ሸምበቆዬን ጌታ አልሰበርክም

የወደቀውን አይተህ መች ተውከው ጌታ

አጸናንተህ አቆምከው ሆንክለት መከታ

አመሰግንሃለሁ(፫)

ስትረዳኝ/ስትራራልኝ በዓይኔ ስላየሁ

አመሰግንሃለሁ(፪)

ዕለት ዕለት ፍቅርህ ሁልጊዜ አዲስ ነው

ጉልበት ትሆናለህ ለደካከመው

እንደ ንስር ኃይሉን ታድሰውና

ዳግም ታቆማለህ በሕይወት ጐዳና

Waaqayyoo siin galatee ffadha

ስለውለታህ ላመስግንህ

ስለማዳንህ ላመስግንህ

ስለጥበቃህ ላመስግንህ

ስላደረክልኝ ላመስግንህ

ስለውለታህ ላመስግንህ

ስለማዳንህ ላመስግንህ

ስለሰራህልኝ ላመስግንህ(፪)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ