አትፈርብኝ
Ateferebegn
2012 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ በዘመኔ አትፈርብኝ ጌታ በእኔ(፫)
ኢየሱስ በዘመኔ አትዘንብኝ ጌታ በእኔ(፫)
አዝማች · Chorus
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና አገልግሎቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ኑሮዬን
(ይኽው) ይኽውና እየው
ቁጥር 2 · Verse 2
በስምህ አጋንንት ቢወጣ
በስምህ ሽባ ቢንተረተር
ዘምሬ ቅኔን ተናግሬ
ተዓምራቶችን ሁሉ አድርጌ(፪)
ዓመጸኛ ተብዬ ከአንተ እንዳታርቀኝ
አቤቱ ዘመኔን በእጅህ አርግልኝ አብጀው(፪)
አዝማች · Chorus
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና አገልግሎቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ኑሮዬን
(ይኽው) ይኽውና እየው
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤቱ በዘመኔ አትፈርብኝ ጌታ በእኔ(፫)
ኢየሱስ በዘመኔ አትዘንብኝ ጌታ በእኔ(፫)
የሰጠኸኝ ፀጋ ስጦታ
መች ሰጋህ እኔ እንዳልወጣው
እንዳሰብከው እንዳቀድክልኝ
እንዳገለግልህስ ከመረጥከኝ(፪)
አቤቱ መንፈሴን በመንፈስህ ቃኘው
የስሜቴን ሳይሆን የአንተን ልናገረው(፪)
አዝማች · Chorus
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና አገልግሎቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ሕይወቴን
(ይኽው) ይኽውና እየው
(ይኽው) ይኽውና ኑሮዬን
(ይኽው) ይኽውና እየው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ