ረቢ ሆይ
Rebi Hoy
2012 · ትራክ 4 · አማርኛ
ከእግርህ ስር ሆኜ ልማር ቃልህን
ከእግርህ ስር ሆኜ ልወቅ ቃልህን
ረቢ ሆይ(፪)
(ረቢ ሆይ) ና አስተምረኝ
(ረቢ ሆይ) በቃልህ
(ረቢ ሆይ) መንገዴን አቅና
(ረቢ ሆይ) ከሕይወት ቃልህ(፪)
ቃልህ ለመንገዴ ለሕይወቴ ብርሃን ነው
ይህን ክፉ ዘመን የማልፈው በአንተ ነው
በሚገባኝ መንገድ ና አስተምረኝ
የሕይወትን መንገድ አቅጣጫን አሳየኝ(፪)
ቃልህ ይብራልኝ ጌታ(፪)
እንድኖር ሁሌ በእርጋታ
ቃልህ ይብራልኝ ጌታ(፪)
ቃልህን ያገኘ ልቦናው ይበራል
ጥበብ እያበዛ በክብር ይዘልቃል
ጥፋት አያገኘው ሕይወት የሚገታ
እርስቱን ይወርሳል የማታ የማታ(፪)
ቃልህ ይብራልኝ ጌታ(፪)
እንድኖር ሁሌ በእርጋታ
ቃልህ ይብራልኝ ጌታ(፪)
ከእግርህ ስር ሆኜ ልማር ቃልህን
ከእግርህ ስር ሆኜ ልወቅ ቃልህን
ረቢ ሆይ(፪)
(ረቢ ሆይ) ና አስተምረኝ
(ረቢ ሆይ) በቃልህ
(ረቢ ሆይ) መንገዴን አቅና
(ረቢ ሆይ) ከሕይወት ቃልህ(፪)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ