Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሳቤን ፈውሰው

Hasaben Fewesew

2012 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ለስሜቴ ለሥጋዬ

ለራሴ ለፍላጐቴ

አትስጠኝ(፫) ቸሩ አባቴ

ሃሳቤን ፈውሰው(፪)

ክፋትን ለማድረግ ቁጭ ብዬ ባስበው

በመኝታዬ ሆኜ ባሰላስለው

ነግቶ ላላደርገው ዋስትና የለኝም

ኃይልም በእጄ ነው ከቶ አያቅተኝም

ሃሳቤን ፈውሰው (፪)

ክፉ አድራጊዎችን አንተ ትጠላለህ

የጠማማውን መንገድ ትቃወመዋለህ

አልሁንብህ ጌታ እንደምትጠላቸው

የድርጊቴ ምንጩን ሃሳቤን ፈውሰው

ሃሳቤን ፈውሰው (፪)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ