Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ ግን ያው አንተ ነህ

Ante Gen Yaw Ante Neh

ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አይገልጽህም የእኔ ቃላት

አይገልጽህም የእኔ አንደበት

ዘውትር ለአንተ ልስገድልህ (ልስገድልህ)

ልቀኝልህ ልሁን በፊትህ (ልሁን በፊትህ) (፪x)

(አንተ) ስትሰራ የኖርክ ከጥንት ጀምሮ

(አንተ) ሥራህ አዲስ ነው መቼ ተቆጥሮ

(አንተ) ሁሌ አዲስ ነህ አዲስ ነህ ለእኔ

(አንተ) አትለመድም ጌታዬ በእኔ (፪x)

አትለመድም ጌታዬ በእኔ (፫x)

አትለመድም አትለመድም ልዩ ለእኔ (፪x)

በምድር ክበብ ላይ ጌታ ተቀምጠሃል

ፍጥረት በመገረም ተሞልቶ ያይሃል

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለና የነበርክ

የእኔም ጉልበት ለአንተ በፊትህ ይንበርከክ

ለሥምህ ይንበርከክ

አንተ ያው አንተ ነህ (አንተ)

አንተ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ) (፪x)

ጌታ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ጌታ ያው አንተ ነህ (ጌታ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

አይገልጽህም የእኔ ቃላት

አይገልጽህም የእኔ አንደበት

ዘውትር ለአንተ ልስገድልህ (ልስገድልህ)

ልቀኝልህ ልሁን በፊትህ (ልሁን በፊትህ) (፪x)

(አንተ) አንተን ያወቀ የተረዳህ

(አንተ) እንዴት ይችላል ሳያመልክህ

(አንተ) ፍቅር እኮ ነህ ፍቅር ነህ ጌታ

(አንተ) በምንም ነገር የማትተካ (፪x)

አንተ ያው አንተ ነህ (አንተ)

አንተ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ) (፪x)

ጌታ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ጌታ ያው አንተ ነህ (ጌታ)

ኢየሱስ ያው አንተ ነህ (ያው አንተው ነህ)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ