Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

Anten Metebeq Bezu Terf Alew

ትራክ 12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው

አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም

በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም

አንተን ጠብቆ ባዶ የቀረ

መከራ ገጥሞት የተማረረ

አላየሁኝም አልሰማሁኝም

ያለፈው ዘመን ታሪክ ይመርመር ከቶ አይገኝም

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው

አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም

በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም

ሥጋ ለባሹን የተደገፈ

በሰው ስራ ላይ አይኑ ያረፈ

ምርኩዙ ሲወድቅ እሱም ወደቀ

አንተን ያለው ግን የማታ ማታ ደስ ብሎት ሳቀ

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው

አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም

በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም

እኔም ባለፈው ሰውን አይቼ

ተጎድቻለሁ መንገዴን ስቼ

ከእንግዲህ አንተን እጠብቃለሁ

ዛሬ ባለቅስም የማታ ማታ እኔም ስቃለሁ

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው

አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም

በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም

የእምባዬ ፍሬ ለምልሞ ባላይ

ቢያጠወልገው የበጋው ፀሀይ

የመጨረሻው ዝናብ ይዘንባል

የእኔም ፈተና ከነኮተቱ ገደል ይገባል

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው

አንተን ጠብቆ ያፈረ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ