ትሻለኛለህ አባባ
Teshalegnaleh Ababa
ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሊያጠግብ ኩርማን እንጀራ
ቀንና ሌሊት ብሰራ
አለቀ ኃይሌ ጉልበቴ
በክንድህ ጥቂት ዘመኔ
በአንተ ቤት ልረፍ መድህኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከዛሬ ነገ ይሻል ብዬ
ብዙ ሮጥኩኝ ጨርቄን ጥዬ
በዓለም ያየሁት አበሳ
እስከመቼም አይረሳ
ከእንግዲህ በቃ ሩጫዬ
መስቀልህ ሆኗል ምርጫዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
ቁጥር 3 · Verse 3
ክፉ ዓለም ክብር የጐደላት
ጦር እንጂ ሰላም የሌላት
ሰው በአምላክ አምሳል ተፈጥሮ
ወደ አውሬነት ተቀይሮ
እርስ በርስ ስታብላላ
በውሸት ዕውቀት አታላ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
ቁጥር 4 · Verse 4
የዚህ ዓለም ጌታ ከመሆን
ሰማይን ምድርን ከመግዛት
እራስን ላንተ አስገዝቶ
ድሃ ተብሎ መጠራት
ክብር እንደሆነ አወቅሁ ጠንቅቄ (፪x)
በቤትህ ልኑር ማቅቄ
አዝማች · Chorus
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ