ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ያያሉ
Aynochu Bemeder Hulu Yayalu
ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ምስኪኖችን ይወዳል
ጐስቋሎችን ይወዳል
ሰው የጣለውን ያነሳል
የተረሳውን ያስታውሳል
ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ያያሉ
ለዓይነስውራን መሪ ነው
ለአካለ ስንኩል ድጋፍ ነው
ለረሃብተኞች መጋቢ
ወላጅ አልባውን ሰብሳቢ
ለደሃ አደጐች አባት ነው
ለመበለቶች ዳኛ ነው
ሃዘንተኛውን ያጽናናል
ጌታ ለሁሉም ይሆናል
ጌታ ሰርግ ቤት ይገኛል
ውሃውን ወይን ጠጅ ያደርጋል
በለቅሶም በሀዘን ቦታ
ተገኝቶ ያጽናናል ጌታ
ህመመተኛውን ደጋፊ
አስታማሚ አልጋ አንጣፊ
ሐኪም ነው በሽታን ያውቃል
ፈዋሽ ነው ነጻ ያወጣል
ካህን ነው ሕዝብን ይመራል
ንጉሥ ነው ያስተዳድራል
ወታደር ነው አገር ጠባቂ
ከአውሬ ከአንበሳ ነጣቂ
አገር ሲወረር በግፍ
ሕዝብ እንደ ቅጠል ሲርግፍ
ከምስኪኖች ጐን ይቆማል
መርከቡን በባሕር ያሰጥማል
ሃዘን ትጥቅህን አይፍታ
ችግርክን ንገር ለጌታ
አያልፍም ከንፈሩን መጥጦ
ያነሳል እጅን ጨብጦ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ