በእግዚአብሔር ዓለም
BeEgziabhier Alem
2014 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር አንደመኖር
በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር አንደመኖር
ቁጥር 1 · Verse 1
እወደዋለሁ ሕይወቴን የለወጠው
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
በአንተ ዘንድ ያለን የህይወት ቃል
ሌላ ስፍራ የትም ማላገኘው
ብር የማይሰጠኝ ወርቅ የማይሰጠኝ
የሕይወቴን አቅጣጫ የለወጠው
የሁልጊዜ ነው የልቤ ሰላም
ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨው
ቁጥር 2 · Verse 2
በዚህ አለም ነገር የማይወሰን
የእኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው
ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ
ብዙ ሰላም አለ በሕይወቴ
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ
መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ
ሸክም የከበደው ወደ እኔ ይምጣ
ይረፍ ብለህ የጠራኸኝ አንተ እኮ ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁሉንም ነገር ለ አንተ ሰጥቼ
እፎይ ብዬ ተደላድዬ ምኖርብህ
ኢየሱስ ከአንተ ጋር ያለኝ ህብረት
ማለት ለእኔ አለሜ ነው
ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት
ምክኒያቱ ነው የዘላለሜ የሰመረበት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ