Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኢየሱስ የሚለው ስም

Eyesus Yemilew Sem

2014 · ትራክ 7 · 5:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እየሱስ የሚለው ስምህ

ልዩ ትርጉም አለው ለእኔማ

ስጠራው ስደጋግመው (፪x)

መጽናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ!

ከፍታዬ ነው መነሻዬ ነው ሆ!

መጽናኛዬ ነው መበርቻዬ ነው ሆ!

ከፍታዬ ነው ስሙ እየሱስ የሚለው

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ

እጠራዋለው እጠራዋለው እየሱሴን

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ

ከሞት ያዳነኝን ሕይወት የሰጠኝን የታደገኝን

እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ (፬x)

በስምህ ውስጥ አለ ሰላም

በስምህ ውስጥ አለ

በስምህ ውስጥ አለ በረከት

በስምህ ውስጥ አለ

በስምህ ውስጥ አለ ኃይል

በስምህ ውስጥ አለ

እየሱስ እየሱስ በእምነት ላለ

ከሞት የሚያስጥል

(አንተን) ደብቄ እንኳን እራሴን ላሳይ

(እየሱሴ) እንደው በአጋጣሚ ስምህን ሲያነሱ ሳይ

(እየሱሴ) እንባ ይቀድማኛል ምሆነውን አጣለሁ

(እየሱሴ) ፊቴ ድቅን ይላል ያረክልኝ ሁሉ

(እየሱሴ) ቆሜ አደባባይ ገና አወራዋለው

(እየሱሴ) በስምህ አላፍርም አለም ሁሉ ይስማው

(እየሱሴ) ክብርስ ቢሉ የቱ ክብሬ ነው

(እየሱሴ) ሁሉን ያገኘሁት ስምህን አምኜ ነው

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ

እጠራዋለው እጠራዋለው እየሱሴን

እጠራዋለው እጠራዋለው ይህን ስምህ

ከሞት ያዳነኝን ሕይወት የሰጠኝን የታደገኝን

በስምህ ውስጥ አለ ሕይወት

በስምህ ውስጥ አለ

በስምህ ውስጥ አለ ክብር

በስምህ ውስጥ አለ

በስምህ ውስጥ አለ ስልጣን

በስምህ ውስጥ አለ

እየሱስ እየሱስ በእምነት ላለህ

ታሪክ የሚቀይር

ስምህ መፍትሄ ነው ለጥያቄ ሁሉ

(እየሱሴ) ኧረ ማን አፍሯል በስምህ ተማምኖ

(እየሱሴ) የስምን ጉልበት እኔም አውቀዋለው

(እየሱሴ) በስምህ ታምኜ ያለፍኩት ስንቱን ነው

(እየሱሴ) ለሞተው ነገር ሕይወት የሰጠህ

(እየሱሴ) ያበቃው ነገር ተስፋ እየቀጠለ

(እየሱሴ) ብዙዎች ሲጠፉ በሕይወት ያለሁት

(እየሱሴ) ታምኜው ነው ስምህን እዚህ የደረስኩት

እየሱስ እየሱስ ብዬ ስለው ብዬ ስለው

ሃይሌ ይታደሳል በረታለሁ በረታለሁ

እየሱስ እየሱስ ብዬ ስለው ብዬ ስለው

ከክብር ወደ ክብር እሻገራለሁ እጨምራለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ