ለካ ምሕረትህ ነው
Leka Mehereteh New
2014 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በምሕረትህ ነው በምሕረትህ /2
ቆም ብዬ አሰብኩና የትላንትናውን
ቆም ብዬ አስተዋልኩት ያለፈው ታሪኬን
ቆም ብዬ አሰብኩና የትላንትናውን
ቆም ብዬ እኔ አስተዋልኩት ያለፈው ታሪኬን
ለካ ምሕረትህ ነው እኔን ሰው ያረገኝ
ለካ ይቅርታህ ነው በሕይወት ያኖረኝ
ለካ የጨለመው ድቅድቁ ሌሊቴ
ለካ በምሕረትህ ነው የነጋው አባቴ
አዝማች · Chorus
አመልክሃለሁ ከልቤ
አመልክሃለሁ አምላኬ
አመልክሃለሁ በደስታ
አመልክሃለሁ የኔ ጌታ
የመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ
የሕይወቴ ዋና አንተ ነህ
ደስታን ያየሁብህ አንተ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሕይወቴ ፍስሐ አንተ ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንድ ሁለት ብዬ ምቆጥረው ከራሴ የሆነ
አንድም ነገር የለም እኔ አረኩት የምለው
የሆነልኝ ሁሉ ባንተና ካንተ ነው
ክብርህን አልወስድም እንዲያው እጭምራለሁ
አዝማች · Chorus
አመልክሃለሁ ከልቤ
አመልክሃለሁ አምላኬ
አመልክሃለሁ በደስታ
አመልክሃለሁ የኔ ጌታ
የመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ
የሕይወቴ ዋና አንተ ነህ
ደስታን ያየሁብህ አንተ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሕይወቴ ፍስሐ አንተ ነህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ያለ ምሕረትህ ያለ አንተ ይቅርታ
ዛሬ አልደርስም ነበር ርህራሄህ ባይበዛ
እጄን በጅህ ይዘህ እየመራኸኝ
ያባትነት ፍቅርህ እዚህ አደረሰኝ
አዝማች · Chorus
አመልክሃለሁ ከልቤ
አመልክሃለሁ አምላኬ
አመልክሃለሁ በደስታ
አመልክሃለሁ የኔ ጌታ
የመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ
የሕይወቴ ዋና አንተ ነህ
ደስታን ያየሁብህ አንተ ነህ
ቁጥር 6 · Verse 6
ከመሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ
ቁጥር 7 · Verse 7
ለካ ምሕረትህ ነው እኔን ሰው ያረገኝ
ለካ ይቅርታህ ነው በሕይወት ያኖረኝ
ለካ የጨለመው ድቅድቁ ሌሊቴ
ለካ በምሕረትህ ነው የነጋው አባቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ