በረከቴ ኢየሱስ ነው
Bereketie Eyesus New
2014 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በስጋም በነፍስም የባረከኝ (፪x)
ደጋግሞ የባረከኝ
በልጁ በኢየሱስ የባረከኝ (፪x)
ደጋግሞ የባረከኝ
ጌታ አልበቃህም ወይ ባርከኽኝ (፪x)
እኔ እንኳን ብል በቃኝ
አንተ መቼ እረካህ ባርከኽኝ (፪x)
እኔ እንኳን ብል እፎይ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሀዘን የሌለበት በረከት ደስታ ብቻ የሆነ
እየሱስን ሰጥተህ ባርከህኛል በል ሂድ ልጄ ብለህ
ሀዘን የሌለበት በረከት ደስታ ብቻ የሆነ
ኢየሱስን ሰጥተህ ባርከህኛል ተከናወን ብለህ
አዝማች · Chorus
በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (፫x)
በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
አንዴ የሚወጣ ተመልሶ ደግሞ አንዴ የሚወርድ
አይደል በረከቴ በምድር እንዳለው የሚመጣ የሚሄድ
እየሱስን ሰጥተህ አንዴ ዘላለሜን አባ ባርከኽዋል
እጠቀመዋለው መንዝሬ መንዝሬ
እንኳን ለእኔ ለአለም ሁሉ ይበቃል
አዝማች · Chorus
በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (፫x)
በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
በሰማዩ ስፍራ በመንፈሳዊ ሁሉ በረከት ባረከኝ
በልጁ በኢየሱስ ሥምም ስላመንኩኝ ሁሉን አወረሰኝ
የእርሱን በጐነት የእርሱን መልካምነት ለዓለም አወራለው
በረከቴ ኢየሱስ የጐደለኝ የለም አንተን ስላገኘው
የኔማ የኔማ በረከት ሰላም የሞላበት ደስታ የሞላበት
እየሱስ ያለበት
የእኔማ የእኔማ በረከት የተትረፈረፈ ፈጽሞ የማያልቅ
እየሱስ ያለበት
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ ያለበት (፯x)
ሰላም የሞላበት
ኢየሱስ ያለበት (፯x)
ኢየሱስ ያለበት
በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (፫x)
በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ