Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በመንፈስህ እንጂ

Bemenfesih Enji

2024 · 5:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

በፊቴ የቆመው ታላቅ ተራራ

አታልፉም ብሎ የሚያስፈራራ

ተደላድሎልን የተሻገርነው

ጌታ ሆይ በኃይልህ ነው

ከእኛ ነው ብለን የምንቆጥረው

በዘመናችን እስቲ የቱን ነው

ሁሉንም መልካም አድርገሃልና

ይሁን ለአንተ ምሥጋና

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

አንድ ሁለት ብለን ዘመን ቆጥረናል

ክፉና ደጉን ሁሉን አይተናል

ዛሬ ላይ ቆመን ስናስተውለው

የአንተ ፀጋ ብዙ ነው

ኧረ እንዴት ብለን ደረስን እዚህጋ

መስሎን ነበር ሌቱ የማይነጋ

ማይቻለውን ላስቻልከን ጌታ

ይሁንልህ ዕልልታ

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

የሄድንባቸው ረጅም መንገዶች

ያለፍንባቸው እነዚያ ቀኖች

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነውና

ይሁንልህ ምሥጋና

በሕይወት እንድንኖር ምክንያት የሆነን

ከብዙ ጉዳት ጥፋት ያዳነን

የአንተ ብርቱ ክንድ ነውና

ይሁን ለአንተ ምሥጋና

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

በመንፈስ እንጂ መች በብርታት

በመንፈስ እንጂ መች በጉልበት

በመንፈስ እንጂ መች በዕውቀት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ