የሕይወት ውኃ
Yehiwot Wiha
2024 · 5:54 · አማርኛ
የእኔ ሙግት የእኔ ክርክር
ማንነቱን ሳልውቀው ነበር
የሕይወቴ ቁልፍ በእጁ እንዳለ
ያስተዋልኩት ዘግይቼ ነበር
ጉዴን ውስጤን አውቆ የነገረኝ
ወደ ሕይወት መንገድ የመለሰኝ
ለካስ ይሄ ጌታ ኢኢየሱስ ነው
ማን መሆንህን አውቄያለሁ
የሕይወት ውኃት ሰጣለህ
አንተ የምትሰጠውን የሚጠጣ
ዳግም እንዳይጠማው ታረካለህ
ኢየሱስ የሕይወት ውኃ ነህ
ከያዕቆብ ጉድጓዶች የመነጨ ውሃ
ከቶ አያሻግርም የዓለምን በረሃ
አንተ ግን ኢኢየሱስ የምትሰጠው
ለዘላለም ሕይወት የሚያዘልቅ ነው
የዘላለም ነው
ማን መሆንህን አውቄያለሁ
የሕይወት ውኃት ሰጣለህ
አንተ የምትሰጠውን የሚጠጣ
ዳግም እንዳይጠማው ታረካለህ
ኢየሱስ የሕይወት ውኃ ነህ
ከሰማይ ወረደ የሕይወት እንጀራ
ዘላለም እንድኖር ከእርሱ ስበላ
ወዶ በፈቃዱ ራሱን አቀረበ
ደግ ቸር ጌታዬ ለነፍሴ ያሰበ
ለነፍሴ ያሰበ
ከእንግዲህ ከአንተ ወደት እሄዳለሁ
ከአንተ ወዴት
የሕይወት ውኃ መሆንህን አውቄያለሁ
ከአንተ ወዴት
እኔማ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ከአንተ ወዴት
የሕይወት ቃል መሆንህን አውቄያለሁ
ከአንተ ወዴት
ከእንግዲህማ ከአንተ ወደት እሄዳለሁ
ከአንተ ወዴት
የሕይወት ውኃ መሆንህን አውቄያለሁ
ከአንተ ወዴት
እኔማ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
ከአንተ ወዴት
የሕይወት ቃል መሆንህን አውቄያለሁ
ከአንተ ወዴት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ