ማደሪያው
Maderiyaw
2024 · ትራክ 7 · 5:30 · አማርኛ
በልቤ አድሮ የነበረ ኮተታ ኮተት ቆሻሻው
ተጠርጐ ወጣ ለቀቀ ስፍራውን ለሚገባው
ታጠበ ጸዳ አማረ ተሸላለመ ለጌታ
ንጉሤን ሾምኩት በልቤ ሳመልከው በደስታ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ውዴ በበር ላይ ቆሞ ሲያንኳኳ ደጄን ሲመታ
የሕይወት እንጀራን ይዞ አዘጋጅሮልኝ ገበታ
ነፍሴን ሊያጠግባት ከፍቅሩ ዘልቆ ሲገባ ከቤቴ
ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ተቀያየረ ሕይወቴ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ቃሉን ገለጠ ለነፍሴ የጌታ መንፈስ መምህሩ
ገብቶኛል ተረድቻለሁ ለካስ እንዲህ ነው ነገሩ
ውዴ ሆኖኛል ለእኔ እኔም ለእርሱ ሆኛለሁ
ለሌላው እንዳልሆን ሆኜ በቃል ኪዳን ታስሬያለሁ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ማደሪያው መቅደሱ አደረገኝ
ለክብሩ ለየኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ