አለቴ
Alete
2024 · ትራክ 6 · 5:01 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዓለቱ ላይ የቆመ ቤት አለኝ
መሠረቱ እጅግ እጅግ የጸና
በቀላሉ የማይገፋ የማይወድቅ በጊዜያዊ ፈተና
ቢጐርፍም ጐርፉ በላዬ ቢነፍስብኝም ነፋሱ
አንድ ነገት ግን ገብቶኛል አይችልም ሊለየኝ ከእርሱ
ቢጐርፍም ጐርፉ በላዬ ቢነፍስብኝም ነፋሱ
አንድ ነገት ግን አውቃለሁ አይችልም ሊለየኝ ከእርሱ
አዝማች · Chorus
አለቴ መሠረቴ
ኢየሱስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ
አለቴ መሠረቴ
ክርስቶስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ የእግዚአሔር ልጅ ነው ጉልበቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ያመንኩትን ማን እንደሆን አውቃለሁ
ተፈትኖ አልፏል በመከራ
በድካሜ ከቶ ማይፈርድብኝ
ይልቅ ለእኔ የሚያስብ ነው ሚራራ
ሞትስ ቢሆን ወይንስ ሕይወት
ከፍታ ቢሆን ዝቅታ
ይህንን ተረድቻለሁ አይችል ሊለየኝ ከጌታ
ሞትስ ቢሆን ወይንስ ሕይወት
ከፍታ ቢሆን ዝቅታ
ይህንን ተረድቻለሁ አይችል ሊለየኝ ከጌታ
አዝማች · Chorus
አለቴ መሠረቴ
ኢየሱስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ
አለቴ መሠረቴ
ክርስቶስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ የእግዚአሔር ልጅ ነው ጉልበቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጸንቶ ቆሟል እግሬ በጌታዬ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ በቃሉ ላይ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
አልነዋወጥም ሰድጃለሁ ስሬን
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
ንፋስ ዓይነቅለኝም ሰድጃለሁ ስሬን
ጸንቶ ቆሟል እግሬ በጌታዬ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ በቃሉ ላይ
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
አልነዋወጥም ሰድጃለሁ ስሬን
ጸንቶ ቆሟል እግሬ
ንፋስ ዓይነቅለኝም ሰድጃለሁ ስሬን
አዝማች · Chorus
አለቴ መሠረቴ
ኢየሱስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ
አለቴ መሠረቴ
ክርስቶስ ሕይወቴ
አለቴ መሠረቴ
ጌታ የእግዚአሔር ልጅ ነው ጉልበቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ