በዘላለም ዙፋን ላይ
Bezelalem Zufan Lay
ትራክ 2 · 6:17 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘንዶውን ገጠመክ አሸነፍክ ጌታ
በኃይል በሰልፍም የምትበረታ
ፅኑ ሀያላንን ሁሉ ያሸነፍክ
የኃያል ኃያል ኢየሱስ ብርቱ ነህ
አዝማች · Chorus
በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃይልህ ከኃያላን ሁሉ ይበልጣል
ውሀን እንደ ግንብ ቀጥ አድርጎ ያቆማል
ከአጥፊዎችም እጅ ክንድህ ያስጥላል
የይሁዳ አንበሳ ማን ይመስልሀል
አዝማች · Chorus
በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃይልህን ሳያውቁ የተነሱብህ
አስከትተው ጦር የዘመቱብህ
ክንድህ ገጥሟቸው ተሸንፈዋል
ሥራቸው ጠፍቶ አንተ ነግሰሀል
አዝማች · Chorus
በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰማይ ምድርን በስልጣንህ ቃል
ፍጥረት አስኪደነቅ ሰርተሀቸዋል
ስላልተገኘልህ ከቶ ላንተ አቻ
ሥምህ ገነነ እስከ ምድር ዳርቻ
አዝማች · Chorus
በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ