እግዚአብሔር ትቶኛል
Egziabhier Tetognal
ትራክ 3 · 7:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 1 · Verse 1
ለአንቼ የገባሁትን የተስፋ ቃሌን
ምነው በጥቂቱ ተጠራጠርሺኝ
በሃዘን አልቅሰሽ ለምን አስጨነቅሺኝ
ስለምንስ ልጄ ጌታ ረሳኝ አልሺኝ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚያጽናናኝ የለም መንገድ ዳር ጥሎኛል
እግዚአብሔር እንደሰው ፊቱን ከእኔ አዙሯል
ተለዋዋጭ አምላክ እንደሰው ሆነብኝ
ብለሽ አምተሽኛል ጌታዬ እንኳን ጣለኝ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 3 · Verse 3
በሃዘን ቀጠረኝ በድካም ከበበኝ
ፍርዴን አጣመመው ምድረ በዳ ተወኝ
በሙላት ከቤቴ ወደ እርሱ መጣሁኝ
ባዶዬን አስቀረኝ ስለምንስ አልሽኝ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 4 · Verse 4
ጉድጓድ እንድትገቢ ጠላት ከማሰልሽ
ከእሳት አውጥቼሽ ከመቼው ተረሳሽ
እስቲ መለሽ ብለሽ ባርኮጽህን ቁተሪ
እባክሽን ልጄ እንዲህ አታምርሪ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 5 · Verse 5
አጭር ዝምታዬ ነው ወይ ያስመረረሽ
ጭር ያለው በረሃ ያጣልኩ ያስመሰለሽ
በክረምቱ ዝናብ እረሰርስሻለሁ
ያስጨነቀሽንም ሁሉ ገስጻለሁ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ
የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ
ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም
ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም
ቁጥር 6 · Verse 6
እስቲ አመስግኒኝ ማልቀሱን ተይና
ጠላትሽን በፊቴ አሳፍሪውና
በቤትሽ በጓዳሽ ሁሉ እገባና
አነቃሻለሁ ዳግም እሰራሽና
ተመስገን ኢየሱስ ስላሰብከን
ተመስገን ጌታ ሆይ ስላየኸን
ተመስገን ኢየሱስ ስላሰብከን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ