Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብርሀን በራ

Birhan Berra

2026 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ደመናማ ቀን ፀሀይ ፈራች ልታይ ቁስሉን

የእግዚአብሔርን ልጅ ያንን መልካም የፍቅር ልክ

አብ አንድያ ልጁን ሰጠን ለእኛ መስዋዕት ሊሆን

በመስቀል ሞቶ አወረደዉ ምህረቱን

ያየ ሲፅፈው ደግሞ ሲያወራዉ

ሲያወራ የሰመ ላልሰማ አሰማ

ላመኑበት ግን ብርሀን በራ

ላመኑበት ግን ብርሀን በራ

ማነህ ሞት መውጊያህ የታል

በደሙ ተሸንፈሀል

ማነህ ሞት መውጊያህ የታል

በደሙ ተሸንፈሀል

የይስሀቅ ምትክ የመስዋዕቱ በግ

ኢየሱስ መጣ እኛን ሊታደግ

ከሌዊ የሚበልጥ የዘላለም ክህነት

ለሚያምንበት ሁሉ ነው ማምለጫ ከሞት

ዳግም ላንፈራ ዳግም ላንሰጋ

አስተማመነን የክርስቶስ ስራ

ማነህ ሞት መውጊያህ የታል

በደሙ ተሸንፈሀል

ማነህ ሞት መውጊያህ የታል

በደሙ ተሸንፈሀል

የይስሀቅ ምትክ የመስዋዕቱ በግ

ኢየሱስ መጣ እኛን ሊታደግ

ከሌዊ የሚበልጥ የዘላለም ክህነት

ለሚያምንበት ሁሉ ነው ማምለጫ ከሞት

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ