Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መልካም ነገር

Melkam Neger

2026 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መልካም ነገር ተገኘለት ሙት ለሆነው

ተራውን ሰው በመንፈስህ አከበርከው

ትርጉም የለው ህይወቴ ካንተ ሌላ

ምርጫዬ ነህ የእድሜ ዘመን መደምደሚያ

የሀጥያቴን ብዛት ቆጥረህ ብትፈርድብኝ

ከስፍር ለሚልቅ በደሌ ምትክ ባትልክልኝ

ብትተወኝ ለራሴ ባትገባልኝ ጣልቃ

ያለቀለት ነበረ ህይወቴ ለሞት የሚያበቃ

ምህረትህ ብርታቴ ከፊት ባይቀድምልኝ

እልፍ ቸርነትህ ቅጥርን ባይቀጥረኝ

ባትይዘኝ በእጆችህ በክንፎችህ ጥላ

ምን ነበር ተስፋዬ ባትሆነኝ ከለላ

መልካም ነገር ተገኘለት ሙት ለሆነው

ተራውን ሰው በመንፈስህ አከበርከው

ትርጉም የለው ህይወቴ ካንተ ሌላ

ምርጫዬ ነህ የእድሜ ዘመን መደምደሚያ

በሰዎች መሰፈርት -ብዙዋች እያሉ

ደካማን መምረጥህ ይገርመኛል -ከሃያላን ሁሉ

እኔ ምን እላለሁ -አንተ ካደረከው

ለፀጋህ ክብር እና ምሰጋና- ዘለአለም እሰዋለሁ

ምህረትህ ብርታቴ ከፊት ባይቀድምልኝ

እልፍ ቸርነትህ ቅጥርን ባይቀጥረኝ

ባትይዘኝ በእጆችህ በክንፎችህ ጥላ

ምን ነበር ተስፋዬ ባትሆነኝ ከለላ

መልካም ነገር ተገኘለት ሙት ለሆነው

ተራውን ሰው በመንፈስህ አከበርከው

ትርጉም የለው ህይወቴ ካንተ ሌላ

ምርጫዬ ነህ የእድሜ ዘመን መደምደሚያ

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ