ትልቅ
Tiliq
2026 · ትራክ 3 · አማርኛ
መግቢያ · Intro ×2
ትውልድ ማዳንህን ሁሌ ይናገራል
ትልቅነትህን ዘውትር ይዘምራል
የዘመን መቀየር ምንም ያለወጠህ
የእድሜዎችህ ብዛት ከቶ ያላስረጀህ
አዝማች · Chorus ×2
ትልቅ ህያው አምላክ እግዚአብሔር አንተ ነህ
ለዘመንህ ቁጥር መለኪያ የሌለህ
የሙዚቃ ክፍል · Instrumental
---
ቁጥር 1 · Verse 1 ×2
ከአማልክት መሃል እንዳንተ ያል የለም
ዙፋንህ የጸና ንጉስ ነህ ዘላለም
ሃይልና ብርታትህ ማን ይስትካካላል
በሰማይ በምድር ማንስ ይመስልሃል
አዝማች · Chorus ×2
ትልቅ ህያው አምላክ እግዚአብሔር አንተ ነህ
ለዘመንህ ቁጥር መለኪያ የሌለህ
የሙዚቃ ክፍል · Instrumental
---
ድልድይ · Bridge
የዘመን መቀየር ምንም ያለወጠህ
የእድሜዎችህ ብዛት ከቶ ያላስረጀህ
ፍጡር ባንተነትህ ሲደነቅ ይኖርል
ትልቅነትህን ዘውትር ይዘምራል
አዝማች · Chorus ×2
ትልቅ ህያው አምላክ እግዚአብሔር አንተ ነህ
ለዘመንህ ቁጥር መለኪያ የሌለህ
የሙዚቃ ክፍል · Instrumental
---
ቁጥር 2 · Verse 2
ማንነትህ ረቂቅ የማትተነተን
ፍጹም ሃያል አምላክ የማትባል ለምን
ግርማና ዉበትህ ማይደረስበት
ትልቁ ስራህን የማይመረምሩት
አዝማች · Chorus ×2
ትልቅ ህያው አምላክ እግዚአብሔር አንተ ነህ
ለዘመንህ ቁጥር መለኪያ የሌለህ
የሙዚቃ ክፍል · Instrumental
---
መዝጊያ · Outro ×2
ትልቅ ህያው አምላክ እግዚአብሔር አንተ ነህ
ለዘመንህ ቁጥር መለኪያ የሌለህ
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ