Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ችላ አትበል

Chila Atibel

1997 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል

ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ

አያዋጣም እዚም እዚያም

መረጋገጥ እንዲያው መዋተት

ትርፉ ሞት ነው ተው ወንድሜ

አያዛልቅ በኃጢአት መዋኘት

ወስነህ ተቀበል ጌታን በልብህ

ኃጢአት አያባብለህ ጨክነህ ተወው ተወው ይቅርብህ

ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል

ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ

የዓለም ኑሮ እሽኮለሌው

እያሳሳቀ ወደ ሞት ነው

ይልቅ ንቃ ዛሬ ወስን

ሞት እንደው ቀጠሮ የለው

ለሕይወትህ ሰላም አግኝ እረፍትን

ና ብሎ ሲጠራ ዛሬ ነገ አትበል ስጠው ልብህን

ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል

ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ

ሀብት ቢሞላ ቢትረፈረፍ

ለነፍስ አንድም ጠብታ የለው

አንተነትህን የሚያረካ

ካለ ኢየሱስ ሁሉም ዘበት ነው

እረኝነቱ ሥር መጥተህ ተጠለል

ኢየሱስን ምረጠው ለነፍስ ለሥጋህ ሌላ ሌላ አትበል

ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል

ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ

ና ወደ እርሱ ጌታ ይፈታል

አንተነትህን ይለውጣል

በአዲስ ሕይወት በአዲስ ኑሮ

ልብህን ደስታ ይሞላል

ሰላምህ እንደ ወንዝ ሞልቶ ይፈሳል

ዋጋ አትከፍልበትም ወስን ወንድሜ ጌታ ይሻላል

ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል

ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ

ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ