እንደገና-በጊዜው ደረሰልኝ
Endegena
1997 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ
ዳግም ተስፋዬን አደሰው
እንባዬን ካይኔ አበሰው
አምላኬ ታሪኬን ለዋወጠው
እንደገና እንደገና እንደገና
እንደገና አቆመኝ /(፪x)
የኤርትራ ባህር በፊቴ እኔን ሊውጥ አፍጥጦ
የጠላቴ ጦር ከኋላ ሰይፉን መዞብኝ መጥቶ
ተስፋ ቆርጬ ስጨነቅ ጌታ ድንቅ አደረገ
የኤርትራን ባህር ከፍሎ እኔን በዚያ አሻገረ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
በመንገዴ ላይ የቆመ ታላቅ ግዙፍ ተራራ
ቢገፉት የማይገፋ በሚያማርር መከራ
ተሻግሮ ማለፍ አቅቶኝ ኃይሌም ከውስጤ አልቆ
ኢየሱስ ከፊቴ አራቀው ሙቱን ተስፋዬን አደሰው
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
የሕይወት ዘመኔ መንምኖ ሞትም ዙሪያዬን ከቦኝ
ቀኔን ስጠብቅ ባልጋ ላይ ሕመም በጣም ጸንቶብኝ
እጅግ ቆዝሜ ሳነባ ደረሰልኝ አባባ
አዋጅን በአዋጅ ሻረ ሕይወትን ለኔ አበሰረ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃብቴ ንብረቴ ሁሉ አልቆ ዘመድ አዝማድም ርቆኝ
ከቁስሌ የተነሳ ሰው እጅጉን ተፀይፎኝ
ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር እንደገና አሰበኝ
ሕይወቴን አረሰረሰ ዳግም ምርኮዬን መለሰ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ
ዳግም ተስፋዬን አደሰው
እንባዬን ካይኔ አበሰው
አምላኬ ታሪኬን ለዋወጠው
እንደገና እንደገና እንደገና
እንደገና አቆመኝ /(፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ