Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ደስ የሚልህን ስጦታ

Des Yemilehen Setota

2005 · ትራክ 3 · 4:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ደስ የሚልህን ስጦታ

በእጄ ያለኝን ጌታ

ራሴን ላድርግ መስዕዋትህ

ከሁሉ በላይ የምሰጥህ

ኑሮህን ጨርሰህ በእኔ ኑር

ካሰብከው የሚቀርህ አይኑር (፪x)

በአንተ መኖር ያሰብከውን መኖር

ኑሮህን መኖር መርጫለሁ

ብኖር ለአንተ

ብሞትም ለአንተ

ከፈቃድህ ስር ይሁን መቃብሬ

ከዚህ ሌላ ኑሮ/ሕይወት አይታየኝም እኔ (፪x)

በላይ ያለው ፈቅድህ

በምድር በእኔ እንዲሆን

ይኸው ራሴን አምጥቻለሁ

ለአንተ እንዲሆን ሰጥቻለሁ

ለክብርህ መገለጫ ዕቃ

የወደድከውን ማድረጊያ (፪x)

እንደ ወትሮው በሥጋዬ

ከብሮ ሳየው ውድ ጌታዬ

ልጁን በእኔ መልክ ገልጦት

ያሰበውም ሰምሮለት

ደስታዬ ያን ጊዜ ይሞላል

መሻቴ ፍጻሜን ያገኛል (፪x)

በአንተ መኖር ያሰብከው መኖር

ኑሮህን መኖር መርጫለሁ

ብኖር ለአንተ

ብሞትም ለአንተ

ከፈቃድህ ስር ይሁን መቃብሬ

ከዚህ ሌላ ኑሮ/ሕይወት አይታየኝም እኔ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ