Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እርስቴ ነህ

Erestie Neh

2005 · ትራክ 7 · 6:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተ ላወቁብህ ክብር ነህ

የማዕረግ መጐናፀፊያ

የሃዘኑ ዘመን ማስረሻ

ከማይነጥፍ ሰላም መድረሻ

በዕረፍት ወንዝ ዳር ይተከላል

ያገኘህ ከምንጭ ዳር ይኖራል

ዕርዳታው ከሰማይ ደጅ

ይወርዳል የእግዚአብሔር/የአምላኩ እጅ (፪x)

እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ

ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ

ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ

ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ

ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (፪x)

በሰማይ በምድር ማይገኝ

ቢተካስ በሌላ ማያሰኝ

መኖሪያህ በብርሃናት ውስጥ

ውበት ነህ ለርስትህ ጌጥ

ለዘለዓለም ትኖራለህ

ማያረጁ ዓመታት ይዘህ

ለሁሌ ነህ የነፍሴ/የእኔ ምርጫ

ከአዕላፋት አግኝተህ ብልጫ (፪x)

እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ

ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ

ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ

ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ

ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (፪x)

ለሰማይ ዉበትን የሰጠህ

ለምድር ዳርቻን ያበጀህ

እኔን በአምሳልህ መፍጠርህ

የከበርሁ አርገህ ማየትህ

ልቤ በመደነቅ ተሞላ

ክብሬ ሊያዜምልህ ተነሳ

ከልብ የሚፈልቅ ምሥጋና

መስዋዕቴ ወደ ላይ ይግባ (፪x)

እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ

ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ

ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ

ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ

ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ