Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስትወድ ብዙ

Setewed Bezu

2005 · ትራክ 1 · 7:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስትወድ ብዙ ስትምር ብዙ

ደግነትህ አበዛዙ

መልካምነትህን ለእኔ አልቆጠብከው

ለያንዳንዱ ነገር አብዝተህ አየሁ

ከለመንኩህ እና ካሰብኩት በላይ

ሁሉ ተከናውኖ ተደርጎልኝ ሳይ

ምለውን አጣሁ ዝም አሰኘኝ

የአንት ስራ አስደነቀኝ (፪x)

ከተደረገልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር

እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ

አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (፪x)

ኃይሌ እንዳልል አይደል ብዙ

ብልጠት በዝቶ አልደርስኩ

ለእኔ አንተ በርትተህ ተናጥቀህልኛል

በርትተህ ተዋግተህ ምርኮን በዝብዘሃል

እንካ ምሥጋናዬን ላንት ላብዛ ላብዛ

ሳልጠግብ ውዳሴህም አፌን ከቶ አልዝጋ

ወዳጄ ነህ የምወድህ

ከሁሉ በላይ የማበልጥህ (፪x)

ከተደረገልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር

እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ

አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (፪x)

ሙት ነበርሁ የማረባ

ከመንደሬ ስትገባ

ምን ነበረኝና ምኔን ወዶ ልበል

የትኛው እኔነቴ ለዚ ሳበው ልበል

እንዲያው ቸርነትህ ያ ፍቅርህ ካልሆነ

አይገባኝም መድሃኒቴ የእኔ ጌታ

የአንተ ውለታ (፪x)

ከተደረገልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር

እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ

አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ