ኤልሮኢ
Elroee
6:25 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሄድኩበት መንገድ ሁሉ ከእኔ ጋራ ለነበረው
ያንን ገደላገደሉን ተሸክሞኝ ላሻገረኝ
እኔን በእቅፉ ሰብስቦ ባላንጣዬን ላሳፈረ
ምስጋናዬ አይነስበት ልወድሰው በዝማሬ
ደስታዬን በፊቱ ገልፃለው
እንዴትስ ችዬ ዝም እላለሁ
ያደረገልኝን እያሰብኩ በልዑል አምላክ ፊት ሰግዳለሁ
አዝማች · Chorus
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
እቶኑ እጥፍ ቢነድም እንዳይፈጀኝ ተጠንቅቆ
ያለእርሱ ምንም እንዳልችል ገና አስቀድሞ አውቆ
በለቅሶ ፈንታ ደስታ በሃዘን ምትክ እፎይታ
የለወጠልኝ አምላኬ ይክበርልኝ የእኔ ጌታ
ደስታዬን በፊቱ ገልፃለው
እንዴትስ ችዬ ዝም እላለሁ
ያደረገልኝን እያሰብኩ ለልዑል አምላክ ፊት እቀኛለሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንቆቅልሽ ለበዛበት ለእዚህ ታናሽ ብላቴና
ከአንበሳ ከድብ ሲታገል ኃይል ሲያንሰው አየውና
የሚያበረታ መብልን ልኮ ቀሰቀሰውና
ረዥም መንገድ ያቋርጣል በአምላኩ እየተፅናና
ደስታዬን በፊቱ ገልፃለው
እንዴትስ ችዬ ዝም እላለሁ
ያደረገልኝን እያሰብኩ ለልዑል አምላክ እቀኛለሁ
አዝማች · Chorus
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የጠራኝ አምላክ ታማኝ ነው ፍፁም አደራን አይበላም
በእርግጥ ቃሉን ያከብራል ቃልኪዳኑን አያጥፈውም
የተናገረውን ፈፅሞ ዘወትር ሲከበር ይኖራል
እኔም እድል ፈንታ አለኝ ልቀኝለት ይገባኛል
ደስታዬን በፊቱ ገልፃለው
እንዴትስ ችዬ ዝም እላለሁ
ያደረገልኝን እያሰብኩ ለልዑል አምላክ እቀኛለሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ደስታዬን በፊቱ ገልፃለው
እንዴትስ ችዬ ዝም እላለሁ
ያደረገልኝን እያሰብኩ ለልዑል አምላክ እቀኛለሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
ኤልሮኢ ኤልሮኢ የሚያየኝን አየሁ
የሚያየኝን አየሁ
የሚያየኝን አየሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ