Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ

Track 7

4:44 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ

ነፍሳችን ረካች በጉብኝትህ

ጥያቄያችንም ተመለሰልን

ስምህ ይባረክ ከፍ ይበልልን

ጠላት ጠፍሮ ፍፁም ተብትቦ

እንዳናመልክህ ዙሪያው ተክቦ

መሰንቆአችንን ከሰቀልንበት

ዛሬ አውርደን ንገሥ አልንበት

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ

ነፍሳችን ረካች በጉብኝትህ

ጥያቄያችንም ተመለሰልን

ስምህ ይባረክ ከፍ ይበልልን

እኛስ ቆዝመን አዝነንም ነበር

ማየት ተስኖን ከሞት ባሻገር

በትንሳኤው ኃያል ደስታን ሞልተኸን

በባዕድ ምድር እንዘምራለን

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ

ነፍሳችን ረካች በጉብኝትህ

ጥያቄያችንም ተመለሰልን

ስምህ ይባረክ ከፍ ይበልልን

ከአቻምና አምና ከአምናም ዘንድሮ

የአንተ ቸርነት ስንቱ ተቆጥሮ

ስንቱን ጨለማ አሸጋገርከን

ከምንገምተው በላይ ሆንክልን

እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ

ነፍሳችን ረካች በጉብኝትህ

ጥያቄያችንም ተመለሰልን

ስምህ ይባረክ ከፍ ይበልልን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ