እንዳልሸበር
Endalesheber
2006 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዳልሸበር እንዳልፈራ
ከፊቴ ወጥቶ ከእኔ ጋራ
አባቴ ጀግና ደግሞ አሸናፊ
እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ
እኔም ልጁ ነኝ አሃ አሃ ድልን አድራጊ (4x)
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ገናና ነው
ገናና ነው
መንግስቱ ወደር የለው
ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው
እርሱ የበላይ ነው (4x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃይላት ሥልጣናት ሁሉንም ገፎ
ድል አስለመደኝ ለእኔ ተዋግቶ
ፅኑ ቃልኪዳን ከእኔ ጋር ገብቷል
ጠላቴ ዛሬ መርዶውን ሰምቷል
ጠላቴ ዛሬ አሃ አሃ መርዶውን ሰምቷል (4x)
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ገናና ነው
ገናና ነው
መንግስቱ ወደር የለው
ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው
እርሱ የበላይ ነው (4x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፍታ ነው እንጂ አይደለም ዝቅታ
ለእኔ ያየው ጌታ (2x)
ድርሻዬ ነው ለኔስ ሁልጊዜ ከፍታ
ለእኔ ያየው ጌታ (2x)
እንዳልሸበር እንዳልፈራ
ከፊቴ ወጥቶ ከእኔ ጋራ
አባቴ ጀግና ደግሞ አሸናፊ
እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ
እኔም ልጁ ነኝ ድልን አድራጊ (4x)
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ገናና ነው
ገናና ነው
መንግስቱ ወደር የለው
ከሁሉ እርሱ የበላይ ነው
እርሱ የበላይ ነው (4x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ