ያለኝ ኢየሱስ ነው
Yalegn Eyesus New
2006 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዚች አጭር ዘመን ስንቱን አየሁባት
እንደ እየሱስ ያለ ፈልጌ አጣሁባት
እውነተኛ እርካታ ከእርካታም በላይ
እንደ እየሱስ የለም በምድርም በሰማይ
አዝማች · Chorus
እርካታዬ ጌታዬ እርካታዬ/4
ያለኝ ከምንም ከማንም ያለኝ ለኔ ሚጠጋጋ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የህይወቴ ቤዛ
ያለኝ መከታና ጋሻ ያለኝ ለጥም እርካታዬ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የዋርካ ጥላዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
አለም ያለው ሁሉ ሁሉም ነገር ከንቱ
ካንተ ጋር መጣበቅ ማትረፊያ መንገዱ
እኔስ አልከሰርኩም አንተን አንተን ብዬ
ፀጋ በዝቶልኛል ይልቁን ጌታዬ
አዝማች · Chorus
እርካታዬ ጌታዬ እርካታዬ/4
ያለኝ ከምንም ከማንም ያለኝ ለኔ ሚጠጋጋ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የህይወቴ ቤዛ
ያለኝ መከታና ጋሻ ያለኝ ለጥም እርካታዬ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የዋርካ ጥላዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለሰው ልፋቱ እንዲ ትርፉ ልፋቱ ነው
ተረጋግቶ መኖር በእየሱስ ብቻ ነው
እኔም ተረጋጋው ከቃሉ ሰምቼ
እድል ፈንታዬ ነው ላምልከው ከልቤ
አዝማች · Chorus
እርካታዬ ጌታዬ እርካታዬ/4
ያለኝ ከምንም ከማንም ያለኝ ለኔ ሚጠጋጋ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የህይወቴ ቤዛ
ያለኝ መከታና ጋሻ ያለኝ ለጥም እርካታዬ
ያለኝ እየሱስ ብቻ ነው ያለኝ የዋርካ ጥላዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ