የበላይ ነው ጌታ
Yebelay New gieta
2006 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እየሱሴ የኔ ጠበቃዬ ለኔ
እየሱሴ የኔ ዋስትናዬ ለኔ
ዋስትናዬ ለኔ ዋስትናዬ ለኔ/2
ጠበቃዬ ለኔ ጠበቃዬ ለኔ/2
ቁጥር 1 · Verse 1
አንድ ነገር ገባኝ ከቃሉ ተረዳው
እግዚአብሔር ትልቅ ነው ማነው የእርሱ ከልካይ
ቢተክል ቢነቅል ሲያሻው ቢገነባ
ተው የሚለው የለም የበላይ ነው ጌታ
የበላይ ነው ጌታ/4
አዝማች · Chorus
እየሱሴ የኔ ጠበቃዬ ለኔ
እየሱሴ የኔ ዋስትናዬ ለኔ
ዋስትናዬ ለኔ ዋስትናዬ ለኔ/2
ጠበቃዬ ለኔ ጠበቃዬ ለኔ/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ወደሰማይ ቢኬድ ምድርን ቢዞር
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም አይገኝ
ፍጥረታትን ሁሉ እርሱ ያስተዳድራል
ስሙ ድንቅ መካር የበላይ ተብሏል
የበላይ ተብሏል/4
አዝማች · Chorus
ከጠላቴ በላይ የበላይ የሆነው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
እየሱስ ጌታ ነው ጠላቴን አልፈራው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ከሁኔታ በላይ የበላይ የሆነው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ጥሼው እሄዳለው ሁኔታን አልፈራው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁኔታ ቢያስፈራ ምድር ብትናውጥ
የማመልከው አምላክ ፈፅሞ አይለወጥ
ከከበበኝ በላይ ጌታዬ በላይ ነው
ባስጨነቀኝ ሁሉ የበላይ ጌታ ነው
የበላይ ጌታ ነው/4
አዝማች · Chorus
እየሱሴ የኔ ጠበቃዬ ለኔ
እየሱሴ የኔ ዋስትናዬ ለኔ
ዋስትናዬ ለኔ ዋስትናዬ ለኔ/2
ጠበቃዬ ለኔ ጠበቃዬ ለኔ/2
ቁጥር 4 · Verse 4
ስጋለባሽ ሁሉ በፊቱ ዝም ይበል
ግዜው የእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ይናገር
እግዚአብሔር ሲናገር ሁሉ ይገለበጣል
የቆመው ተራራ በፊቴ ዝቅ ይላል
በፊቴ ዝቅ ይላል/4
አዝማች · Chorus
ከጠላቴ በላይ የበላይ የሆነው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
እየሱስ ጌታ ነው ጠላቴን አልፈራው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ከሁኔታ በላይ የበላይ የሆነው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ጥሼው እሄዳለው ሁኔታን አልፈራው
አለና የበላይ የሆነው አለና የበላይ የሆነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ