የሕይወት ቃል አለህ
Yehiwot Qal ALeh
2006 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ካንተ ወደማህ እሄዳለው አንተ የህይወት ቃል አለህ
ዘመኔን በሙሉ ሰጠሁህ ጌታዬ አንተ የህይወት ቃል አለህ
የህይወት ምንጭ ነህ ጌታ ለተጠማው አንተ የህይወት ቃል አለህ
ምንጭህን አፍልቀህ ጌታ ታረካለህ አንተ የህይወት ቃል አለህ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሰላሜ ነህ አንተ እየሱስ
እረፍቴ ነህ አንተ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ እየሱስ አንተ ትመቻለህ አንተ የፍቅር ቃል አለህ
ልገልፅህ ብሞክር ካይምሮ በላይ ነህ የሱስ የምትገርም አምላክ ነህ
ማለዳ ስነሳ ሁልግዜ አዲስ ነህ አንተ ዘላለም ልዩ ነህ
ፍጥረት ተሰብስቦ ድንቅ ነህ ይበልህ አሜን እየሱስ ድንቅ ነህ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሰላሜ ነህ አንተ እየሱስ
እረፍቴ ነህ አንተ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደሃጥያቴ ብዛት አልፈረድክብኝም አንተ የምህረት አምላክ ነህ
ቸርነትህ ብዙ እየሱስ መልካም ነህ አንተ ከሰው ትለያለህ
እንደሃጥያቴ ብዛት አልፈረድክብኝም አንተ የምህረት አምላክ ነህ
ቸርነትህ ብዙ እየሱስ መልካም ነህ አንተ ከሰው ትለያለህ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሰላሜ ነህ አንተ እየሱስ
እረፍቴ ነህ አንተ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ እየሱስ እረፍቴ ነህ አንተ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ