እጠብቅሃለሁ
Etebkhalew
5:39 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ራቅም አልልም ማንንም ፍለጋ
እጠብቅሃለሁ እኔም እስኪነጋ/2
እንዳንተ አምላኬ ማንም አይሆነኝም
እጠብቅሃለሁ አንተ ብትዘገይም/2
ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ
እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ
ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ
እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ
አዝማች · Chorus
አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ዝም ብትለኝም አውላላ ሜዳ ላይ
ለበጎ ይሆናል አላማህ በኔ ላይ
ምንም ቢደርስብኝ አላማርርህም
እምነቴ ሊፈተን ችግርን ያየህልኝ
ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ
እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ
ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ
እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ
አዝማች · Chorus
አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ሰጠን እግዚአብሔር ወሰደው
አላጉረመርምም ፃድቅ ነው በስራው
አምላኬ ትልቅ ነው ስንፍና አላወራም
ስርዓቱን እንድማር ቢያስጨንቀኝም
ዛሬም ቢሆን ነገም እጠብቅሃለሁ
እንዳማትጥለኝ እኔ አምንሃለሁ
ዛሬም ቢሆን ነገም እታገሃለሁ
እንዳማትረሳኝ በእውነት አምንሃለሁ
አዝማች · Chorus
አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደተናገረው ቃል እንደገባልኝ
አደርጋለሁ ብሎ ተስፋ እንደሰጠኝ
እንዲሁ እንዳለው እንደሚያደርግልኝ
አልጠራጠርም ጌታን አምናለሁኝ
አዝማች · Chorus
አይረሳ አይጥልም ጌታ ለዘላለም/2
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ