ዛሬም ክበርልኝ
Zarem Kiberlgn
6:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔ አምልክሃለሁ በደስታ
ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2
ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን
አስረስተኸኛል መከራዬን/2
ክፉ ያልኳቸውን ቀኖች አሳለፍከኝ
በእጆችህ ደግፈህ ዛሬንም አቆምከኝ/2
ምህረት ቸርነትህ እየተከተሉኝ
በክንፎችህ ጥላ በቤትህ አለሁኝ/2
አዝማች · Chorus
እኔ አምልክሃለሁ በደስታ
ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2
ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን
አስረስተኸኛል መከራዬን/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ለክፉ የተመኘኝ ሊያጠፋኝ የወጣ
አፍሮ ተመለሰ ቃል ካፍህ ሲወጣ/2
ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊቴ ወጣና
ከፍታውን ሰጠኝ አስረገጠኝና/2
አዝማች · Chorus
እኔ አምልክሃለሁ በደስታ
ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2
ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን
አስረስተኸኛል መከራዬን/2
ቁጥር 3 · Verse 3
ዳግም ላይታሰብ የትላንቱ ችግር
እልፍ አደረገኝ ወዳየልኝ ክብር/2
በዙሪያዬ ከበው ነፍሴን ግራ ያጋቡ
ዛሬ አጣኻቸው ወዴት እንደገቡ/2
አዝማች · Chorus
እኔ አምልክሃለሁ በደስታ
ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2
ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን
አስረስተኸኛል መከራዬን/2
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ