ከልጅነቴ ጀምሮ
Keljnete Jemro
5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት
ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2
በእድሜ ቀናቶቼ ሃዘን እንዳይገዛኝ
ምስጋናን ዝማሬን ለእኔ ሰጠህኝ
ትዝታዬ ሆነህ ምሕረትህ ለኔ
ከእጅህ አልጣልከኝም ዛሬም ቢሆን ያኔ/2
አዝማች · Chorus
ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት
ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ከዘመናት በፊት ከእሩቅ ያወቅኅኝ
ገና ሳልፈጠር ዛሬን ያየህልኝ
ለዚያ ለጠላቴ በክፉ ላሰበኝ
አሳልፈህ ለሞት መች እኔን ሰጠሀኝ/2
አዝማች · Chorus
ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት
ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2
ቁጥር 3 · Verse 3
ስቀመጥ ስነሳ ሲጨልም ሲነጋ
ላፍታ ሳትለየኝ ሆነህ ከእኔ ጋር
እንደ አይንህ ብሌን ተጠነከክልኝ
ማንም እንዳይነካኝ ትእዛዝህ ወጣልኝ/2
አዝማች · Chorus
ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት
ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2
ቁጥር 4 · Verse 4
በደሌ ከፍ ብሎ ሳለ
ምሕረትህ በኔ ላይ ገነነ
እኔ ነኝ እግዚአብሔር የረዳኝ
ከትቢያ ካመድ ላይ ያነሳኝ
እኔ ነኝ ጌታ የራራልኝ
እኔ ነኝ ጌታ ሰው ያረገኝ
እኔ ነኝ ይቅር የተባልኩኝ
አዝማች · Chorus
ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት
ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ