Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በጅምር አይቀርም

Bejmr Aykerm

5:20 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቃል አለኝ የሚፈፀም አምላኬ የነገረኝ/3

ህልም አለኝ የሚፈታ ጌታዬ ያሳየኝ/3

በጅምር አይቀርም የኔ ነገር

ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2

እገሰግሳለሁ ወዳየልኝ ክብር

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

ዮርዳኖስ ቢሞላም አይቀርም መሻገር

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

ዘልቄ ሄዳለው በምድሪቱ ስፋት

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

በጅምር አይቀርም የኔ ነገር

ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2

ይጨምራል ገና የቅባቱ ጉልበት

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

አልቆምም ሄዳለው ጌታ ብሏልና

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

አይሆንም አልልም ሆኖ ስለማየው

ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2

በጅምር አይቀርም የኔ ነገር

ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2

አምላኬ ሲጠራኝ ከዛ መንደር

ለትልቅ ቁም ነገር/3

እየሱስ ሲያመጣኝ ከዚያ ሰፈር

ለትልቅ ቁም ነገር/3

ለሚያልፈው ለዚ አለም ነገር

ጨከን በል ልቤ አትሸበር/2

ለምን ተበሳጨ ያ ጠላቴ አይቶ መቀባቴን/3

ስለምን ተመኘው ጠላት ሞቴን አይቶ መቀባቴን/3

ከዚህም የበለጠ ገና አለኝ

አምላኬ እግዚአብሔር ያሰበልኝ/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ