ፍቅርህ ትልቅ ነው
Feqereh Teleq New
2008 · ትራክ 3 · 6:16 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ
አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጸሃፊ መች ጠፍቶ
በምድር ላይ ምሁር ሰው
የአንተን ታላቅነት ጀምሮ አይጨርሰው
መች አንዲህ ይቀላል ስለአንተ ቢባል ቢባል
ቢጻፍልህ ተጀመሮ ቀለም ያልቃል
እኔ ግን አድናቆቴን ለአንተ
ባለኝ በሰጠኸኝ ዜማ
ማወደሴን ማክበሬን አልተውም
ለፍጥረት ሁሉ እስኪሰማ
ጌታዬ ጌታዪ ነህ እያለኩ
ቤትህ ቆሜ እንጓደዳለሁ
ኧረ ልዩ ነህ አንተ እኮ ለእኔ
እንደአንተ የት አገኛለሁ
አዝማች · Chorus
ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ
አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለአንተ ክብር ስልጣን ሞገስ ማንነት
እየተረከ ነው ይኼ ሁሉ ፍጥረት
ይህ ነው እስከዛሬ ከፍጥረት ጀምሮ
አላለቀበትም ስለአንተ ተናግሮ
አቤት ድንቅ ነህ አምላኬ እሄ
ሁሉ ምሥጋናና ስግደት
ያለማቋረጥ ያጐርፍልሃል ፍጥረት ሁሉ ከያለበት
እኔም ተረኛ ነኝ ለአንተ ዛሬ
ፊትህ ለማቅረብ ምሥጋና
ጌታዬ ጌታዪ ነህ እያልኩኝ
ልቀኝልህ እንደገና
አዝማች · Chorus
ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ
አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስከ ዛሬ ስለአረክልኝ ውለታ
አቀርብልህ ነበር ምሥጋናና እልልታ
ስለአረክልኝ አይደለም ምቀኝልህ
ስለደነቀኝ ነው የአንተ ማንነትህ
ተገረምኩ አድናቆት ያዘኝ በአንተ
ማንነትህን አውቄ
እስቲ ጌታዬ ጌታዬ ልበል
በእግሮችህ ስር ወድቄ
ቃላት ያንሰኛል ለመግለጽ የአንተን
ማንነትህ ወደር የለው
. (1) . ፍቅርህ
ስምህ ምሥጋና ይድረሰው
አዝማች · Chorus
ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ
አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ