ቃል ብቻ ተናገር
Qal Becha Tenager
2008 · ትራክ 8 · 9:55 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቃል ብቻ ተናገር (፬x)
የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (፫x)
ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የታመመብኝን ሰው አልጋ ላይ አስተኝቼ
ወደ አንተ መጣሁኝ ሁሉን ነገር ትቼ
ቃልህ ዓይን እንዳለው ስለተማመንኩኝ
መቅደስህ ገብቼ ቃልህን ጠበኩኝ
ተነሳ ከአልጋ ላይ ብለህ እዘዝልኝ
ወዲያው እንደሚነሳ በቃል አምናለሁኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃል ብቻ ተናገር (፬x)
የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (፫x)
ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለሰው ያልነገርኩት ማንም የማያውቀው
እንድ ጉዳይ አለኝ አንተ የምታውቀው
አምላክ ይቻልሃል ለአንተ ሁሉ ነገር
ለችግሬ መውጫ ስለአዘጋጀህ በር
እስከመቼ ድረስ ልሸከም ጥያቄ
ቃል ብቻ ተናግረህ ፍታ እንቆቅልሼን (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃል ብቻ ተናገር (፬x)
የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (፫x)
ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ የቀመስኩትን ሕይወት ያልቀመሱ
በምስራች ወንጌል ገና ያልተደረሱ
በቤቴ ሞልተዋል አንተን ያልተረዱ
ወደ ሞት ጐዳና ዝምብለው ሚነዱ
ዛሬ ቃል ተነገር እንዲለወጡልኝ
ቤቴ ወንጌል ይግባ አንተን/ጌታን ያግኙልኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃል ብቻ ተናገር (፬x)
የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (፫x)
ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰማይና ምድርን በቃልህ አጽንተሃል
ሁኑ ስትል ሆነው በአንተ ተፈጥረዋል
ቃልህ ኃይለኛ ነው ስልጣን የተሞላ
ሰይጣንን የሚጥል እሳት ነው ሚባላ
በሕይወቴ ዘመን የሚያስቸግረኝን
ቃል ብቻ ተናግረህ ጠላቴን/ሰይጣንን ጣልልኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃል ብቻ ተናገር (፬x)
የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (፫x)
ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (፫x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ደረቁን ምድረበዳ ምን ተስኖት
ይሞላዋል በአበባ ምን ተስኖት
የጐደለንን ሁሉ ምን ተስኖት
ያደርግልናል ሙሉ ምን ተስኖት
ለእርሱ የሚያቅት የለም
ይችላል እርሱ ዘለዓለም
ሁሉንም ቻይ ነውና
እናንግሰው በምሥጋና (፪x)
ምን ተስኖት (፬x)
ምን ተስኖት (፬x)
የሞተውን ሬሳ ምን ተስኖት
እናያለን ሲያስነሳ ምን ተስኖት
ለእኛ ያቃተን ሁሉ ምን ተስኖት
ይቻለዋል በእርሱ ምን ተስኖት
ኤልሻዳይ አምላክ ነውና
የሚሳነው የለምና
ምን ተስኖት እንበለው
ድል የሚገኘው ያኔ ነው (፪x)
ምን ተስኖት (፬x)
ምን ተስኖት (፬x)
ምን ተስኖት (፬x)
ምን ተስኖት (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ