Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጋርዳቸው ከመታከት

Gardachew Kemetaket

ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለረጅም ዘመናት ተቆልፎባቸው ኤሄሄ ኤሄሄ ኤሄዉ

የፈርዖን ሠራዊት የሚያንገላታቸው

አሉ የተገፉ ስምህን ለማስከበር ኤሄሄ ኤሄሄ ኤሄዉ

ጌታ ሆይ ገርስሰው የጠላትን መንደር (፪x)

ስለ ሥምህ ተጠልተው ያሉትን በሰንሰለት (፪x)

አብራላቸው ክብርህን ጋርዳቸው ከመታከት

ግንባራቸው ይጠንክር ጠላታቸው ይርበትበት

ለሥምህ ነዉና ልጆችህን አጽና

አንተን እንዲክዱ ባንተ እንዲያማርሩ ኡሁሁ ኡሁሁ ኡሁዉ

ይሸርባል ጠላት ብዙ ነው ምስጢሩ

ምሬት በሕይወታቸው እንዳይሆን ጋርዳቸው ኤሄሄ ኤሄሄ ኤሄው

ፈቃድህ ይፈፀም እንድትከብርባቸው (፪x)

ስለ ሥምህ ተጠልተው ያሉትን በሰንሰለት (፪x)

አብራላቸው ክብርህን ጋርዳቸው ከመታከት

ግንባራቸው ይጠንክር ጠላታቸው ይርበትበት

ለሥምህ ነዉና ልጆችህን አጽና

ጠላትም ይንቀጥቀጥ ይታሰር ምላሱ ኡሁሁ ኡሁሁ ኡሁዉ

ይተብተብ እጅ እግሩ ይቅር መላወሱ

ፍጥረት ሁሉ ይመስክር ስለ ኃያልነትህ እሂሂ እሂሂ እሂ

ይሳቁ በፈርዖን ድል ያርጉ ልጆችህ (፪x)

ስለ ሥምህ ተጠልተው ያሉትን በሰንሰለት (፪x)

አብራላቸው ክብርህን ጋርዳቸው ከመታከት

ግንባራቸው ይጠንክር ጠላታቸው ይርበትበት

ለሥምህ ነዉና ልጆችህን አጽና

ከእንግዲህ ጌታ ሆይ ፀሎታችን ስማ አሀሀ አሀሀ አሀ

ታምነናል በኃይልህ አንተ ነህ አንተማ

እንክትክት ብለዉ የወህኒ መዝጊያዎች ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆች

ያመልኩሃል በክብር በድል ያንተ ልጆችህ (፪x)

ስለ ሥምህ ተጠልተው ያሉትን በሰንሰለት (፪x)

አብራላቸው ክብርህን ጋርዳቸው ከመታከት

ግንባራቸው ይጠንክር ጠላታቸው ይርበትበት

ለሥምህ ነዉና ልጆችህን አጽና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ