ጭንቀቴን ላዋየው
Chenqetien Lawayew
ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማለዳ ስነሳ ጭንቀተን ላዋይህ
ነፍሴን ያዛላትን ችግሬን ላሳይህ
ግራ ቀኝም አልልም ምስጥረኛም የለኝ
ኢየሱስ ፈጥነህ ናና ከሀዘኔ ገላግልኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ምነው መጨነቄ ረዳት እንደሌለው
አሕዛብ ያውቃሉ በአንተ እቅፍ እንዳለሁ
አጥፍቼም እንደሆን ቅጣኝ እንደ ልጅህ
የለፋህብኝ ነኝ ፈሶልኛል ደምህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማለዳ ስነሳ ጭንቀተን ላዋይህ
ነፍሴን ያዛላትን ችግሬን ላሳይህ
ግራ ቀኝም አልልም ምስጥረኛም የለኝ
ኢየሱስ ፈጥነህ ናና ከሀዘኔ ገላግልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በዓይን የማይታዩ ሠራዊቶች አሉኝ
ጠላቴን ከእግሬ ሥር የሚያንጋልሉልኝ
ብዬ ተናግሬ ለዓለም ዙሪያ ሁሉ
አሁን ብንቀጠቀጥ ታድያ ምን ይላሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማለዳ ስነሳ ጭንቀተን ላዋይህ
ነፍሴን ያዛላትን ችግሬን ላሳይህ
ግራ ቀኝም አልልም ምስጥረኛም የለኝ
ኢየሱስ ፈጥነህ ናና ከሀዘኔ ገላግልኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጉድለቱን አውቃለሁ እኔው ነኝ ምክንያቱ
ለስጋም ለነፍሴም እሾህ የሆንኩቱ
አንተ ግን አንተ ነህ ምህረት የተሞላህ
ጠግነኝ በቁጣህ አስተምረኝ እንዳሻህ
አዝማች · Chorus
ማለዳ ስነሳ ጭንቀተን ላዋይህ
ነፍሴን ያዛላትን ችግሬን ላሳይህ
ግራ ቀኝም አልልም ምስጥረኛም የለኝ
ኢየሱስ ፈጥነህ ናና ከሀዘኔ ገላግልኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ