ይሰባሰባሉ
Yesebesebalu
ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ
የተበታተኑት ይሰበሰባሉ
በአንድ ጣራ ሥር ሆነው ዳግመኛ ጌታን ያከብራሉ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አሁን የጨለመ መስሎ ብታየንም
ወጋገን ይወጣል ልናይ ሁሉንም
የገነባው ጠላት ነፋፍቶ ደረቱን
እግዚአብሔር በቃ ስል ይለቃል መንገዱን (፪x)
አዝማች · Chorus
በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ
የተበታተኑት ይሰበሰባሉ
በአንድ ጣራ ሥር ሆነው ዳግመኛ ጌታን ያከብራሉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በስቃይ በሀዘን የተበተኑቱ
በአንድ ልከማቹ ተቃርቧል ሰዓቱ
ሥሙን ልያስከብር ነው ጌታ ተንቀሳቅሷል
የልጆቹን ፀሎት ከፀበዖት ሰምቷል
አዝማች · Chorus
በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ
የተበታተኑት ይሰበሰባሉ
በአንድ ጣራ ሥር ሆነው ዳግመኛ ጌታን ያከብራሉ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀን እንቆጥራለን አንድ ሁሉት ብለን
ጌታ በደጅ ነው ካሳውን ልክሰን
ከአራቱም ማዕዘን ክርቲያኖች ሁሉ
በምድራቸው ጌታን ዳግም ያከብራሉ
አዝማች · Chorus
በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ
የተበታተኑት ይሰበሰባሉ
በአንድ ጣራ ሥር ሆነው ዳግመኛ ጌታን ያከብራሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ