ግራ ቀኝ አልልም
Gera Qegn Alelem
2014 · ትራክ 1 · 6:32 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ግራ ቀኝም አልልም
ወደ ኋላ ወደ ፊት
በአንተ ልቤ እርፍ ብሏል
ሰላም በአንተ አግኝቷል
በጥያቄዬ ሁሉ ጌታ ጣልቃ እየገባ
ነገሬን አሳምሮ ዓይኔ በደስታ አነባ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትላንትናም ዛሬም አንተው ነህ ያለኸኝ
አምናን አሳልፈህ በዚህ ያደረስከኝ
ለነገም አልፈራም አንተ እያለህልኝ
ግራ ቀኝም ሳልል ፀንቼ ቆምኩኝ
ሰላም ሆንከኝ (፫x)
ጌታዬ ሰላም ሆንከኝ
እረፍት ሆንከኝ (፫x)
አባቴ እረፍት ሆንከኝ
ዓይኔን ከሰው አንስቼ አንተን ልመልከት
ብትዘገይም እንኳን መምጣትህ አይቀር
በመንገድህ/በመቅደስህ ቆሜ ጠብቃለሁ
በእርግጥም ስትመጣ በዓይኔ አያለሁ (፪x)
ለምኜ አንድም ቀን አላፈርኩም
ጥያቄም ሞልቶ እርፍ አልኩ
ልቤ በአንተ ዛሬ ተደላድሏል
አንተን አንተን አንተን አንተን ይላል (፪x)
አዝማች · Chorus
ግራ ቀኝም አልልም
ወደ ኋላ ወደ ፊት
በአንተ ልቤ እርፍ ብሏል
ሰላም በአንተ አግኝቷል
በጥያቄዬ ሁሉ ጌታ ጣልቃ እየገባ
ነገሬን አሳምሮ ዓይኔ በደስታ አነባ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰላም ሆንከኝ (፫x)
ጌታዬ ሰላም ሆንከኝ
እረፍት ሆንከኝ (፫x)
አባቴ እረፍት ሆንከኝ
ትላንትናም ዛሬም አንተው ነህ ያለኸኝ
አምናን አሳልፈህ በዚህ ያደረስከኝ
ለነገም አልፈራም አንተ እያለህልኝ
ግራ ቀኝም ሳልል ፀንቼ ቆምኩኝ
ምድረ በዳዬን ታለመልማለህ
ባዶ ሸለቆዬን በውኃ ትሞላለህ
በእርግጥም ኢየሱስ አንተ ታማኝ ነህ (፪x)
ወዳጅ ከአንተ ሌላ ለእኔ ማን አለ
ሚስጥር ተካፋይ አንተ ብቻ ነህ
ሁሉን ነገር አውቀህ ትመዝናለህ
በእውነትም ጌታዬ አንተ ታማኝ ነህ
ወዳጅ ከአንተ ሌላ ለእኔ ማን አለ
ሚስጥር ተካፋይ አንተ ብቻ ነህ
ሁሉን ነገር አውቀህ ትመዝናለህ
በእርግጥም ኢየሱስ አንተ ታማኝ ነህ
ለምኜ አንድም ቀን አላፈርኩም
ጥያቄም ሞልቶ እርፍ አልኩ
ልቤ በአንተ ዛሬ ተደላድሏል
አንተን አንተን አንተን አንተን ይላል
ምድረ በዳዬን ታለመልማለህ
ባዶ ሸለቆዬን በውኃ ትሞላለህ
በእርግጥም ኢየሱስ አንተ ታማኝ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ