ጌታ የእኛ እድል ፈንታ
Gieta Yegna Edel Fenta
1993 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
1. ሕይወት ተገላቢጦሽ ሲሆን ተመስገን
ደስታ ለሓሰተኞች ስትሆን ተመስገን
ሃዘን በእኛ ላይ ሲበረታ ተመስገን
ጉልበት በዝለትም ሲረታ ተመስገን
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
ስንደካክም ብርታት ሆነኸን
ከኃይል ወደኃይል አሸጋገርኸን
እዚህ ደርሰናል ተሸክመኸን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኛ ዕድል ፈንታ
ፍጽም የማትረታ
ስንደክም ስንበረታ
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
እናመሰግንሃለን
ቁጥር 2 · Verse 2
2. መከራ በእኛ ላይ ሲደርስብን ተመስገን
ጠላትም ሲያጠፋን ሲዝትብን ተመስገን
በአውሎ ንፋስ ስትናወጥ ታንኳችን ተመስገን
መልስህ ስታጽናናን ጌታችን ተመስገን
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
ስንደካክም ብርታት ሆነኸን
ከኃይል ወደኃይል አሸጋገርኸን
እዚህ ደርሰናል ተሸክመኸን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኛ ዕድል ፈንታ
ፍጽም የማትረታ
ስንደክም ስንበረታ
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
እናመሰግንሃለን
ቁጥር 3 · Verse 3
3. ዘይትህ በእጅጉ ሞልቶ ሲፈስ ተመስገን
ከእኛ አልፎ ሌሎችንም ሲፈውስ ተመስገን
ዲያቢሎስ ሽንፈቱንም ሲጐነጭ ተመስገን
እኛም እንደ እንድንቦሳ ስንፈነጭ ተመስገን
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
ስንደካክም ብርታት ሆነኸን
ከኃይል ወደኃይል አሸጋገርኸን
እዚህ ደርሰናል ተሸክመኸን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኛ ዕድል ፈንታ
ፍጽም የማትረታ
ስንደክም ስንበረታ
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
እናመሰግንሃለን
ቁጥር 4 · Verse 4
4. ወዳጅ ነው ያሉት ሁሉ ሲርቅ ተመስገን
ከጠላት አብሮ እኛን ሲንቅ ተመስገን
ሁሉ በጊዜው ሲፈራረቅ ተመስገን
አንተ አለኸን በጭራሽ የማትርቅ ተመስገን
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
በድካማችን ብርታት ሆነኸን
ከኃይል ወደኃይል አሸጋገርኸን
እዚህ ደርሰናል ተሸክመኸን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ የእኛ ዕድል ፈንታ
ፍጽም የማትረታ
ስንደክም ስንበረታ
በዚህ ሁሉ ግን አለህ አብረኸን
እናመሰግንሃለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ