ህክምናዬ
Hekemenaye
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ህክምናዬ የኔ መዳኒት/4
ያየኛል እኮ ልቤ ሲንሸራተት
ያየኛል እኮ ሲያቅተኝ ዳገት መውጣት
ያየኛል እኮ ሆድ ሲብሰኝ ስሆን ለብቻ
ያረግልኛል ሁሉንም ያዘን ዳርቻ
ያየኛል እኮ ይሰማኛል እኮ
አላጓድልም በፍፁም የስሙን አምልኮ
የኔ ወጌሻ የኔ ጠጋኝ
በእጁ ታሽቼ ድናለሁኝ
በኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ በቀረ ግዜ
እጄን ሚደግፍ ታማኝ ወዳጅ ባጣሁኝ ግዜ ከቦኝ ትካዜ
ሁሉን ጨርሼ የሚወጣኝን ስጠባብቅ
በተዘጋ በር ከፍቶ የገባ ይዞ ማይለቅ
ደርሶ ያየሁት ብዙ ምህረቱን ታማኝነቱን የማያስነካ
እርሱ እግዚአብሔር ነው በኔ አይምሮ በኔ ትከሻ የማይለካ
ፀንቼ አምናለው ከፊቴ አለ ብዙ መስጋና
ባቃተኝ ጉዳይ በከበበኝ ላይ ይወርዳልና
አዝማች · Chorus
ያየኛል እኮ ልቤ ሲንሸራተት
ያየኛል እኮ ሲያቅተኝ ዳገት መውጣት
ያየኛል እኮ ሆድ ሲብሰኝ ስሆን ለብቻ
ያረግልኛል ሁሉንም ያዘን ዳርቻ
ያየኛል እኮ ይሰማኛል እኮ
አላጓድልም በፍፁም የስሙን አምልኮ
የኔ ወጌሻ የኔ ጠጋኝ
በእጁ ታሽቼ ድናለሁኝ
መፈወሻዬ መጠገኛዬ
መዳኛዬ የሱስ ጌታዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ከሚለኝ ብዙ ካወራኝ ካደካከመኝ ብዙ ውሸት
በለሆሳስ ድምፅ በማውቀው ቋንቋ የተናገረኝ ያምላክ እውነት
እንደመልህቅ አጥብቆ ይዞ ያበረታኛል
እንደማይናወጥ ፀጥ ያለ ባህር ያረጋጋኛል
እስከ ሽበት እስከ ሸምግልና የምሸከምሽ እኔ ነኝ ካለ
ከረግረግ ጭቃ እግሬን ካወጣ ራሴን ሸፍኖ እየከለለ
በእጁ መዳፍ ቀርፆ ከያዘኝ ምን ያሰጋኛል
እምነቴን አልጥል አልደነግጥም የሱስ ያየኛል
አዝማች · Chorus
ያየኛል እኮ ልቤ ሲንሸራተት
ያየኛል እኮ ሲያቅተኝ ዳገት መውጣት
ያየኛል እኮ ሆድ ሲብሰኝ ስሆን ለብቻ
ያረግልኛል ሁሉንም ያዘን ዳርቻ
ያየኛል እኮ ይሰማኛል እኮ
አላጓድልም በፍፁም የስሙን አምልኮ
የኔ ወጌሻ የኔ ጠጋኝ
በእጁ ታሽቼ ድናለሁኝ
መፈወሻዬ መጠገኛዬ
መዳኛዬ የሱስ ጌታዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ